Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

Searching for happiness
Searching for happiness
Searching for happiness
Ebook215 pages1 hour

Searching for happiness

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

The genre of the book is a novel and it explores the journey of three brothers in search of happiness. In particular, the main character, Tanza, has a very challenging and frustrating struggle in his journey in search of happiness.

Languageአማርኛ
Release dateNov 18, 2023
ISBN9798223521082
Searching for happiness
Author

Yeabtsega Ambaw

The author was born in a rural town called Dana in Ethiopia. He has a deep love for literature and is currently studying medicine at university. As a child he loved to read story books and as he got older he started reading fiction books. Because he liked to listen to the legends told in Ethiopia; It is said that he started writing essays based on those legends. Earlier, he published a book called The Search for Happiness, and today he has brought us the next part.

Related to Searching for happiness

Related ebooks

Related categories

Reviews for Searching for happiness

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

1 rating0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    Searching for happiness - Yeabtsega Ambaw

    ልቦለድ

    በየአብፀጋ አምባው

    ሙሉ የባለቤትነት መብቱ የተጠበቀ ሆኖ በፅሑፍ በተሰጠ ፍቃድ ካልሆነ በስተቀር ፤ ይህን መጽሐፍ እንደገና ማሳተም፤ መቅዳት ወይም መተርጎም አይቻልም።

    ምስጋና

    ምዕራፍ አንድ

    ሦስቱ ወንድማማቾች በጣም ፈጣኑ free wifi ባለው እና እጅግ ግዙፍና ቤተመንግስት በሚመስለው መኖሪያቤታቸው ሳሎን ውስጥ ተቀምጠው ስልካቸው ላይ ተጥደዋል። ክረምት በመሆኑና ት/ቤት በመዘጋቱ ታላቅ ወንድማቸው አልሚሪስ ከዩንቨርስቲ ተመልሷል። ሁለተኛው ታላቅ ወንድም መንክር የ 10ኛ ክፍል ውጤት ስላልመጣለት ኮሌጅ ገብቶ ትምህርቱን እየተከታተለ ሲሆን የ ሁለተኛ ዓመት የኮምፒዩተር ሳይንስ ተማሪ ነው ። ሶስተኛውና የሁሉም ታናሽ ታንዛን የ 11ኛ ክፍል ተማሪ ነው ።  ሦስቱም የረፍት ጊዜያቸውን ከቤተሰብ ጋር ለማሳለፍ ቢመጡም ዓይኖቻቸውን ከስልኮቻቸው ስክሪን ላይ መንቀል አቅቷቸው ነው የሰነበቱት። ምሳና ራታቸውን እንኳን ለመመገብ ወደ መመገቢያ ክፍል የሚገቡት በስንት ጭቅጭቅና ንዝንዝ ነው ። ቤቱ ውስጥ የሚዘጋጀው ምግብ ዕንቁላል ጥብስ፣ አሳ ለብለብ፣ ስጋ ጥብስ፤ ዕንቁላል በስጋ፣ ዓይብ በስጋና የመሳሰሉት ቢሆንም የወንድማማቾቹ የምግብ ፍላጎት ከተዘጋ ሰነባብቷል። ሁሉም ነገር እየሰለቻቸው ስንፍናም እየተጫጫናቸው መጥቷል። የቴሌቪዥናቸውን ሪሞት አንስቶ ቻናል ለመቀየር እንኳን የሚሆን ተነሳሽነት በውስጣቸው የለም። አልሚሪስ ቲክቶክ ላይ የሚመጡለትን ቪዲዮዎች ወደ ላይ ወደ ታች እያደረገ ይመለከታል። መንክር አዳዲስ ጌሞችን ከ play store እያወረደ ይጫወታል። ታንዛን ፌስቡክ ላይ ካገኛት ሴት ጋር ይጀናጀናል።  በልጆቻቸው ደስታ ማጣትና ድብርታም መሆን የተጨነቁት ወላጆቻቸው ልጆቻቸውን ለማናገር ይወስናሉ። እናትና አባት ወደ ሳሎን በመምጣት ከልጆቻቸው ፊት ተቀመጡ። አልሚሪስ  ረጅሙ ሶፋ ላይ ተኝቶ ነበር ቲክቶክ የሚመለከተው፤ መንክር ሶፋው ላይ በጀርባው ተንጋሎ ጌም ሲጫወት ፤ ታንዛን የፌስቡክ ጅንጀናውን አጧጡፎታል። ዛሬ እኔና እናታችሁ ልናነጋግራቹ እንፈልጋለን። አለ አባት።  አዎ ዛሬ የቤተሰብ ጉባዔ ይኖረናል ስትል እናት አከለች።  በመጀመሪያ ትኩረት ሰጥታችሁ ታዳምጡን ዘንድ ስልኮቻችሁን አስቀምጡ ። አለ አባት። ነገር ግን እንኳን ስልኮቻቸውን ሊያስቀምጡ የሰሙትም አይመስሉም ነበር ።  እናንተን ኮ ነው ማናግረው ሲል በሀይል አንባረቀባቸው።  አባታቸው ሲቆጣ አይተውት ስለማያውቁ ሁሉም በድንጋጤ ክው ብለው ቀና አሉ። አልሚሪስና ታንዛን ስልኮቻቸውን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጡ። መንክር ግን ጌም መጫወቱን ቀጠለ። ይህንን ያየችው እናቱም ጌሙን ከእጁ ለመንጠቅ እጇን ስትሰድና መንክር ለመከላከል ሲሞክር ስልኩ መሬት ላይ ወደቀ። ደግነቱ ስልኩ ብዙም አልተጎዳም ነበር።  ሺት አስፎረፍሽኝ አለና ፊቱ ላይ ቅያሜውን እንደሳለ ስልኩን ጠረጴዛው ላይ ወረወረና የቤተሰብ ጉባዔውን ለመታደም ዝግጁ መሆኑን አሳየ።  እኔና እና እናታችሁ እዚህ ቤት ደስተኛ እንዳልሆናችሁ እየተሰማን መጥቷል ስለዚህ ደስታችሁን ፈልጋችሁ ታገኙ ዘንድ እንሻለን። አለ አባት ሶስቱንም ልጆቹን በአንክሮ እየተመለከተ።  እኔ ደስታ የሚገኘው በጀብድ ውስጥ ነው ብዬ አምናለሁ ። ተመሳሳይ የሆነ ህይወት አሰልቺ ነው ። ጧት መነሳት ፤ ትምህርት ቤት መሄድ፤ ተመልሶ መተኛት እንደገና ተነስቶ ትምህርት ቤት መሄድ በቃ ተገማች የሆነ ህይወት ይሰለቻል። ስለዚህ መጓዝ ያስደስተኛል ብዬ አስባለሁ ። በጉዞዬ ላይ አዳዲስ ጓደኞች አፈራለሁ። በየደቂቃው ምን ሊያጋጥመኝ እንደሚችል ስለማላውቅ ነገን ላየው እጓጓለሁ። አለ አልሚሪስ።  እኔ ደግሞ ደስታችንን የቀማን ቴክኖሎጂ ነው እላለሁ ፤ ስለዛህ ወደ ገጠር አያቴ ጋ ብሄድ ደስተኛ እሆናለው ብዬ አስባለሁ ። አለ ታንዛን።  አንተስ መንክር? ሲል ጠየቀው የመንክርን ዝም ማለት ያስተዋለው አባት።  እኔ መጀመሪያ ነገር ደስተኛ አይደለሁም ብዬ አላስብም። ደስተኛ ባልሆንም ግድ አይሰጠኝም በማለት ቤተሰቡን በሙሉ አስገረመ።

    ምዕራፍ ሁለት

    መንክር ሶፋው ላይ ጋደም እንዳለ አዲስ ጌም ለማውረድ playstore ገባ። ዕውነተኛ ገንዘብ የሚከፍል ጌም የሚል ፅሑፍ አነበበ። ጌሙን በፍጥነት አወረደው።  ጌሙን ሲከፍተው username እና የ Email አካውንቱን እንዲያስገባ ይጠይቀዋል። የተባለውን ካደረገ በኋላ የስልክ ቁጥሩንና የባንክ አካውንቱን እንዲያስገባ ይጠቀዋል። በድጋሚ የተባለውን ካደረገ በኋላ congratulations you are successfully registered የሚል ፅሑፍ መጣለት። ጌሙን ዳውንሎድ በማድረጉ ቦነስ የአምስት መቶ ብር ካርድ እንደተሸለመ የሚገልፅ ፅሑፍ መጣለት። ባለማመን *804# ደውሎ ሲያረጋግጥ ዕውነትም የአምስት መቶ ብር ካርድ ተሞልቶለታል። መገረም ልቡን ሞላው።

    መንክር በመገረም ወደ ጌሙ ተመለሰ። ጌሙ የሚወደው የመኪና ውድድር ነበር። ጌሙን ተጫውቶ እንዳሸነፈ የቤተሰቦቹን እና የሚወዳቸውን የትምህርት ቤት ጓደኞቹን ስም እንዲሞላ የሚጠይቅ ፅሑፍ መጣ፤ የተሳሳተ መልስ ከሰጠ ክፍያ እንደማያገኝም የሚያስጠነቅቅ ፅሑፍ አብሮት ነበር። የተባለውን አደረገ። 1000 ብር በአካውንቱ ገባለት። ቀጣዩ ጌም አንድን ሞተር ሳይክል ተራራ ማስወጣት ነበር ሶስት ጊዜ ሞክሮ በአራተኛው ተሳካለት። ተከትሎም የ

    የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለበትን ትምህርት ቤት ስም እንዲሞላ ጥያቄ ቀረበለት። ያለምንም ማመንታት ሞላው።

    የ20,000 ብር ሽልማትና አሪፍ የጧት ቁርስ እንደሚዘጋጅለትና ቀጣዩን ጌም ለመጫወት ከ 24 ሰዓት በሗላ እንዲመለስ የሚገልፅ ፅሑፍ መጣለት። በጉዳዩ እየተገረመና ህልምም እንዳይሆን እየፀለየ ወደ መኝታው ሄደ።

    ––––––––

    መንክር ጧት ከዕንቅልፉ ተነስቶ መታጠብያ ክፍል ገባ። በመስታወቱ ፊቱን እያየ ታጠበ። የጥርስ ብሩሽ አውጥቶ ጥርሱን ቦረሸ ።  ድንገት የቤቱ በር ሲንኳኳ ሄዶ ከፈተው። ሙሉ ዩኒፎርም የለበሰ አስተናጋጅ በሰሀን ምግብ ይዞ ቆሟል። 

    ምግብ ታዞ ነበር አለና አስተናጋጁ የያዘውን ሳህን ለመንክር አቀበለው።  ምንም ዓይነት ምግብ ያላዘዘው መንክር ግራ ተጋብቶ አስተናጋጁ ላይ አፈጠጠበት። አስተናጋጁ ግን ሂሳብ እንኳን ሳይጠይቀው ፊቱን አዙሮ ሄደ። መንክር ግራ እንደተጋባ ወደ ቤት ገባ። ሳሎን ገብቶ ምግቡን እንዳስቀመጠ ወደ ስልኩ ሜሴጅ ገባ። ሜሴጁን ከፍቶ ሲያየው 20,000 ብር በባንክ አካውንቱ ገቢ ተደርጎለታል።

    በመደነቅ ትላንት ያወረደውን ጌም ከፍቶ ገባ። ጌሙ የማስጠንቀቂያ ጽሑፍ አመጣለት።

    ቀጣዩ ጌም በመቶ ሺዎች የምትዝቅበት ነው ። ቀጣዩን ጌም ለመጫወት የጌሙን ህግ እንደምታከብር በፊርማህ አረጋግጥ። አንዴ ከፈረምክ በሗላ በምንም ዓይነት ተዓምር ጌሙን ማቋረጥ አትችልም። ይላል ፅሑፉ።

    ––––––––

    መንክር ማስጠንቀቂያውን ችላ ማለት አልፈለገም ነገር ግን የመቶ ሺዎችን ጨዋታም አቋርጦ መውጣቱን አልፈለገም። መወዛገቡ ግልጽ ሆኖለታል። ሁለት ምርጫ አለው አንደኛው መጪውን ጊዜ አደጋ ሊኖረው ይችላል ብሎ በመፍራት ከጨዋታው መውጣት አልያም የመጣው ይምጣ ብሎ ጨዋታውን መቀጠል።

    ቅድም አስተናጋጁ ያመጣለትን የዶሮ ወጥ መመገብ ጀመረ ።

    የኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርቱን ተምሮ ቢጨርስና ቢመረቅ እንኳን በመቶ ሺዎች እንደማይከፈለው ያውቃል። በዛ ላይ ቤቱ ቁጭ ብሎ የሚወደውን ጌም እየተጫወተ ገንዘብ ማግኘቱ አስደሳች ሆኖ አግኝቶታል። ይህንን እያሰበ እያለ ወደ ስልኩ notification ገባለት። ኖቲፊኬሽኑ የመጣው ከጌሙ ነበር። በጌሙ ህጎች መስማማቱን በፊርማው ካረጋገጠ በቀጣይ በሚሊዬኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚያገኝባቸው የጨዋታ ደረጃዎች እንዳሉ የሚጠቁም ፅሑፍ ነበር። ያለምንም ማቅማማት በጌሙ ህጎች መስማማቱን በፊርማው አረጋገጠ።

    መንክር የስልኩ ስክሪን ላይ እንዳፈጠጠ ነው ። ቀጣዩን ጌም ለመጫወት የጌሙን ቁጥር ሁለት ማውረድ እንዳለበት የሚገልፅ ፅሑፍ መጣ። ቀጣዩ ጌም playstore ላይ ስለታገደ ቴሌግራም ቻናል ላይ እንደሚያገኘው በመግለፅ ከፅሑፉ ሥር ሊንኩን አስቀምጦለታል። ሊንኩን ተጭኖ ሲገባ የቴሌግራም ቻናሉ ላይ የተለያዩ ጌሞችን አገኘ። የቴሌግራም ቻናሉ 400,000 ተከታዮች ያሉት መሆኑን አስተዋለ። 400,000 ሰዎች በአሁኑ ሰዓት ጌሙን እየተጫወቱ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገመተ። የጌሙን ቁጥር ሁለት ከቴሌግራም ቻናሉ ላይ በማውረድ install አደረገው።

    ጌሙን ከፍቶ ሲገባ የቅድመን ዓይነት ማስጠንቀቂያ አጋጠመው። በሕጎቹ መስማማቱን confirm የምትለዋን ፅሑፍ በመንካት አረጋግጦ ወደ ጌሙ አለፈ። ጌሙን ከቴሌግራም ቻናሉ ላይ ስላወረደ አምስት ሺህ ብር ወደ ባንክ አካውንቱ እንደገባ የሚያበስር ፅሑፍ ደረሰው።

    በጉጉት የመቶ ሺህ ብር ወደሚያስገኘው የጌሙ ክፍል አለፈ።

    የቀጣዩ ጌም መመሪያ መጣለት።

    " በቀጣዩ ጨዋታ ተጫዋች ከቤቱ ወጥቶ እንዲጫወት ይገደዳል። ጨዋታውንም ካሸነፈ ተጫዋች የመቶ ሺህ ብር ሽልማትና ወደ ቀጣዩ ክፍል የሚያሸጋግረውን የሚስጥር ቁጥር ያገኛል። ቀጣዩ ጨዋታ የሚሊዮን ብሮች ፍልሚያ እንደሆነ ልብ ይሏል።* የሚል ነበር መመሪያው።

    Start የሚለውን ሲጫን መመሪያ ቁጥር ሁለት መጣለት።

    " መመሪያ ቁጥር ሁለት

    ተጫዋች በአውላጥ ከተማ ወደምትገኘው ሙዚየም ካሜራ ይዞ ገብቶ ፎቶ ተነስቶ መላክ አለበት " ይላል ፅሑፉ።

    የማይሞከር  ሲል አሰበ መንክር። በአውላጥ ብሔራዊ ሙዝየም አንድ ጊዜ ብቻ ገብቶ ለመጎብኘት 10,000 ብር ያስከፍላሉ። የሚያገኘውን ሽልማት በማሰብ 10,000 ብር ቢያወጣ ምንም ማለት አይደለም። ነገር ግን ወደ ሙዝየሙ ካሜራ ይዞ መግባት በምንም ዓይነት መልኩ የማይፈቀድ ሲሆን የሚደረግበትን ጥብቅ ፍተሻ አልፎ ካሜራ ይዞ የተገኘ ግለሰብም ከባድ ቅጣት ይጠብቀዋል።

    ይህንን እያሰላሰለ እያለ ሦስት አማራጮች ጌሙ ላይ እንዳለ አስተዋለ።

    Option 1 ጌሙን መቀጠል

    Option 2 ይለፈኝ ማለት

    Option 3 ጌሙን ማቋረጥ

    Option 2ን ተጫነ።

    ወደ ቀጣዩ ክፍል ለማለፍ አንድ ሚሊዮን ብር መክፈል አለብዎት የሚል ፅሑፍ መጣለት።

    ወደ ሗላ ተመልሶ ጌሙን ለማቋረጥ option 3ን ተጫነ።

    ይህንን ጌም ላለማቋረጥ ተስማምተው በፊርማዎ አረጋግጠዋል። ስምምነቱን የሚያፈርሱ ከሆነ በርስዎ ላይ ግድያን ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት ዕርምጃ መውሰድ እንደምንችል ስምምነቱ ይደነግጋል። የሚል ፅሑፍ መጣለት። የስምምነት ፅሑፎችን እስከመጨረሻው ሳያነብ በችኮላ እንደፈረመ ትዝ አለው። በገዛ ዕጁ ወጥመድ ውስጥ እንደገባ ተሰማው።

    ––––––––

    መንክር ከገባበት ድንጋጤ ለመውጣትና ራሱን ለማረጋጋት ሞከረ።

    ስልኩን ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ በረጅሙ ተነፈሰ።

    ቀስበቀስ ድንጋጤውው እየለቀቀው ሲመጣ ከገባበት ወጥመድ ራሱን እንዴት እንደሚያወጣ ማሰብ ጀመረ።

    ምንም ዓይነት ሀሳብ አልመጣልህ አለው።

    በዚህን ጊዜ ስልኩ የማሳወቂያ መልዕክት እንደገባለት አሳወቀው።

    ጠረጴዛው ላይ ያስቀመጠውን ስልክ አነሳ። የአውራ ጣቱን አሻራ በማስገባት ስልኩን ከፈተው።

    የማሳወቂያ መልዕክቱ የመጣው ከጌሙ ነበር። ጌሙን ክፍቶ መልዕክቱን አነበበ።

    *  ተጫዋች በ 48 ሰዓት ውስጥ ጨዋታውን የማይቀጥል ከሆነ ዕርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን።  *  ይላል መልዕክቱ።

    ከመልዕክቱ ሥር ካሜራውን የሚገዛበት ሱቅ አድራሻ ተቀምጧል።

    ከአድራሻው ስር  ከዚህ ሱቅ ብቻ ነው መግዛት የሚቻለው ይላል።

    መንክር ስልኩ ላይ ያለውን የሱቁን አድራሻ ከተመለከተ በኋላ ካሜራውን ለመግዛት በሩን ከፍቶ ወጣ።

    በሩን ከፍቶ ደረጃዎቹን እየወረደ እያለ መንክር ስትል እናቱ ተጣራች።

    ደረጃው ላይ እንዳለ ቆሞ ጠበቃት፤ እናቱ የቤቱን መስኮት ከፍታ ብቅ አለች።

    እኛማ ቤት ተቀምጠህ ድብርት ሊገልህ ነው ብለን ሰግተን ነበር ፤ እንዲህ ወጣ እያልክ አየር ተቀበል። ምንቦጣህ ቤቱ ውስጥ ብቻህን ታፍነህ? አለችው።

    እጁን ለሰላምታ አውለብልቦላት ሊሄድ ሲል እንደገና ጠራችውና አስቆመችው።

    እኔ ምልህ ወንድሞችህ ግን ደውለውልህ ያውቃሉ? ድምፃቸው ጠፋሳ? አለችው።

    ምንም ሳይመልስላት ያገኘውን ታክሲ ተሳፍሮ ሄደ።

    ከታክሲው እንደወረደ ወደ ኤሌክትሮኒክስ መሸጫ ሱቁ አመራ።

    "

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1