Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

The secret wife: ደስታን ፍለጋ, #3
The secret wife: ደስታን ፍለጋ, #3
The secret wife: ደስታን ፍለጋ, #3
Ebook100 pages46 minutes

The secret wife: ደስታን ፍለጋ, #3

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

It is a collection of notes in which Enoch reveals his secret feelings for the king's wife, and in the end, Enoch and Menkar resurrect the Ethiopian queen Saba for a mission.

 

A spirit falls in love with Enoch and tries to entrap him by taking over the bodies of various women. In order not to harm his beloved lover Amu, Enoch is sorely tempted by her flirtatious ways

Languageአማርኛ
Release dateMar 10, 2024
ISBN9798224613472
The secret wife: ደስታን ፍለጋ, #3
Author

Yeabtsega Ambaw

The author was born in a rural town called Dana in Ethiopia. He has a deep love for literature and is currently studying medicine at university. As a child he loved to read story books and as he got older he started reading fiction books. Because he liked to listen to the legends told in Ethiopia; It is said that he started writing essays based on those legends. Earlier, he published a book called The Search for Happiness, and today he has brought us the next part.

Read more from Yeabtsega Ambaw

Related to The secret wife

Titles in the series (2)

View More

Related ebooks

Related categories

Reviews for The secret wife

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    The secret wife - Yeabtsega Ambaw

    ደስታን ፍለጋ ቁ.3

    ሚስጥራዊ ሚስት

    ደራሲ: የአብፀጋ አምባው

    ––––––––

    This is a work of fiction. Similarities to real people, places, or events are entirely coincidental.

    First edition. March 10, 2024.

    Copyright © 2024Yeabtsega Ambaw.

    Written by Yeabtsega Ambaw.

    This book may not be reprinted, distributed, translated or made into a film without the permission of the author

    ሔኖክ

    ኦክሲን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዬሗት ቤተመንግስቱ ውስጥ የተጋጨን ዕለት ነበር ።

    ገና እንዳየሗት ነበር የሆነ የማላውቀው ስሜት የተሰማኝ። የሆነ አለ አይደል ! ብቻ እንግዳ የሆነ ስሜት ። ብቻ ለመግለጽ የሚያስቸግር ዓይነት ስሜት እንበለው።

    ከዛች ቀን ጀምሮ ግራ ገብቶኛል ። ስለዛ እንግዳ ስሜት ማሰላሰል ማቆም አልቻልኩም ። የሆነ ቁርኝት በመካከላችን እንዳለ ዓይነት ነገር ይሰማኛል።  ለምን እንደዚህ እንደሚሰማኝ አላውቅም። ይሔ ነው ብዬ ልገልፀው የማልችለው ዓይነት ስሜት ! ፍቅር ይዞኝ ይሆን እንዴ ? ኦ ! ያ በፍፁም ሊሆን አይችልም ። የሰው ሚስት ያውም የንጉሥ! ለማሰብ መከጀሉ በራሱ ሐጢያት ነው ። ኦክሲን ግን አለማሰብ አልቻልኩም ። በቤተመንግስቱ ውስጥ ስዘዋወር ድንገት ካገኘሗት ሳላስበው ፈገግ እላለሁ። እሷም መልሳ ፈገግ ትልልኛለች። አቤት ፈገግታዋ ሲያምር ።

    ከንጉሥ ሚስት ጋር በድብቅ ፈገግታ መለዋወጥ በራሱ የሆነ ዓይነት ሚስጥራዊ ስሜትን ይፈጥራል ።

    ሁልጊዜ በድብቅ አይቻት ፈገግ ስትልልኝ ይቺ ልጅ ! እላለሁ በሀሳቤ ።

    የምርም ይቺን ልጅ እየተመኘሗት ነው እንዴ? ይሔ እንዴት ሊሆን ይችላል ? ታንዛንን እወደሗለሁ። ዕሙንም እወዳታለሁ ። ነገር ግን ለኦክሲ ያለኝ ስሜት ( የተለዬ ስሜት ለሷ እንደሚሰማኝ እያመንኩ ነው እንዴ ?) ሁሉንም ነገር ያስረሳኛል። ዕሙ ፍቅረኛዬ እንደሆነች ፤ ኦክሲ ደግሞ ንግስቴ መሆኗን እስከመዘንጋት እደርሳለሁ።

    ፍቅር ይዞኛል እያልኳቹ አይደለም። ነገር ግን የሆነ ደስ የሚል ነገር አለው ። ስሙ ምን እንደሚባል አላውቅም። ይሔ እንግዳ ስሜት ፍቅር ከሆነ ራሴን ከዚህ ስሜት እንደማገል አውቃለሁ።

    አለማፍቀር እንደማይቻል ይገባኛል ምክንያቱም ፍቅር ከቁጥጥራችን ውጪ የሆነ ተፈጥሯዊ ክስተት ስለሆነ ። ነገር ግን ልንደብቀው ልንሸሽገው እንችላለን ።

    ቢሆንም ተከድኖ የበሰለ ነገር አንድ ቀን መገንፈሉ አይቀርም ። የገነፈለ ነገር ደግሞ በአቅራቢያው ያለን ነገር መፍጀቱ አይቀርም። ብቻ አለመያዝ ነው ዋናው ፤ አንዴ ከተያዙ መውጫው ከባድ ነው ።

    ታሞ ከመሟቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ይላሉ አበው ሲተርቱ ። ፍቅርን ግን እንዴት ትጠነቀቀዋለህ? በምንስ ጋሻ ትመክተዋለህ?  እንዴትስ እንዳይዝህ ትከላከለዋለህ?

    ከባድ ነው በእውነቱ ፤ ያለኝ አማራጭ ፍቅር እንዳልያዘኝ ማሰብ ብቻ ነው ። ሆ ሆ ከሚያስተዳድረኝ ንጉሥ ሚስት ጋር ፍቅር አላስበውም። እንዴትስ ተደርጎ !? የማይሆነውን ።

    አልጋችን ላይ ጋደም ብዬ በጀርባዋ በኩል የተዘናፈለውን የዕሙን አረንጓዴ ፀጉር እየተመለከትኩ ለኦክሲ ያለኝን እንግዳ ስሜት እያሰብኩ እብሰለሰላለሁ።

    ዕሙ ከጎኔ እንደተኛች እንደመገላበጥ ብላ እጄን ስባ ከጀርባዋ እንዳቅፋት አደረገችኝ። እጆቼ የተራቆተ ዕምብርቷን ሲዳብሱ ይሰማኛል።  ነገር ግን ኦክሲን ካየሁበት ቅፅበት ጀምሮ ለእሙ ያለኝ ስሜት ተቀዛቅዟል። ቀንም ማታም ውስጤ ኦክሲን ኦክሲን ይለኛል። ለራሴም ግራ ገብቶኛል ። እጆቼን አንሸራትቼ የዕሙ ዕጆች ላይ አስቀመጥኩ። ላብ ያጠመቀመው ሞቃት እጅ ነበር የተቀበለኝ። እጆቼን ጨምቃ ይዛ ፊቷን ወደ እኔ አዞረች።

    ሳላስበው ዓይኖቼ ተጨፍነው ኖሯል ። ጣቶቼን ወደ ከንፈሯ አስጠግታ ሳመችኝ። ለምን እንደሆነ ሳላውቀው ተገላብጬ ጀርባዬን ሰጠሗት።

    የተራቆተ ትከሻዬ ላይ ትኩስ ለስላሳ ከንፈር ሲያርፍ ተሰማኝ ። ፊቴን አዙሬ ተመለከትኳት። 

    ኦክሲ ዛሬ ልታገኝህ እንደምትፈልግ ነግራኛለች።

    ይህንን ስትለኝ በድንጋጤ ትን ብሎኝ ልሞት ነበር ።

    ምነው ችግር አለ ? ስትል ጀርባዬን እየደሰቀች ጠየቀችኝ። ዓይኖቿ ውስጥ ጥርጣሬ ያነበብኩ መሰለኝ። አይ የለም ዓይኖቿ ውስጥ ከየዋህነት በስተቀር ምንም አይነበብም። የራሴው ጥፋተኛ ህሊና ነው በዛ መልኩ እንድመለከታት ያደረገኝ። 

    የኔ የዋህ ! ፍቅረኛዋ ከሌላ ሴት ጋር እየማገጠ እንደሆነ አላወቀችም። መማገጥ ግን ምንድነው ?  አንዲትን ሴት አይቶ መመኘትም ያው መማገጥ ነው ። እኔ ግን ኦክሲን አልተመኘሗትም። ሳያት ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ እንጂ። ያ ደግሞ የኔ ጥፋት አይደለም ። ራሴን ለምን ደስ ተሰኘህ ልለው አልችልም ።

    በሚስጥራዊው ዓለም ዕጣ ፈንታ ትልቁን ሚና ይጫወታል ። በሚስጥራዊው ዓለም አስማት እንጂ ሎጂክ ቦታ የላትም። የኛ አለም ለየት ይላል ። ያጠፋ በምድራዊ ሕይወቱ ነው የሚቀጣው። ገሀነም የተባለ የቅጣት ቦታም ሆነ ገነት የሚባል የሽልማት ቦታ የለንም። አጥፊዎቹን የሚቀጡ የሚስጥራዊው ዓለም ጠባቂዎች አሉ። በምድራዊ ሕይወቱ ፍፁም የዋህ እና ደግ የሆነ ፤ የሚስጥራዊውን ዓለም ሕግጋት እስከህይወቱ ፍፃሜ ጠብቆ የኖረ ። እሱ በስተመጨረሻ ሕይወቱ ስታልፍ ከሚስጥራዊው ዓለም ጠባቂዎች እንደ አንዱ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል ።

    የተፈጠረ ችግር አለ ? በማለት ዕሙ አፍጥጣ ጠየቀችኝ ።

    ንግስቲቱ ለምን እንደፈለገቺኝ የምታውቂው ነገር አለ ?? በማለት ጥያቄዋን ወደ ጎን በመተው ጠየኳት ።

    እኔ በምን ላውቅ እችላለሁ ? አለቺኝ ግራ መጋባቷን ፊቷ ላይ እየሳለች ።

    " ምንም

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1