Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

መንፈስ ቅዱስን የሚያገኙበት እርግጠኛውና ትክክለኛው መንገድ: በእኔ ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ
መንፈስ ቅዱስን የሚያገኙበት እርግጠኛውና ትክክለኛው መንገድ: በእኔ ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ
መንፈስ ቅዱስን የሚያገኙበት እርግጠኛውና ትክክለኛው መንገድ: በእኔ ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ
Ebook478 pages3 hours

መንፈስ ቅዱስን የሚያገኙበት እርግጠኛውና ትክክለኛው መንገድ: በእኔ ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

በክርስትና ውስጥ በሰፊው ለውይይት የቀረበ ርዕሰ ጉዳይ ቢኖር ከሐጢያቶች መዳንና መንፈስ ቅዱስን መቀበል ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህን ሁለት ርዕሰ ጉዳዮች በትክክል የሚያውቁ ጥቂት ሰዎች ናቸው፡፡ የሆኖ ሆኖ ሰዎች በተጨባጭ በኢየሱስ እንደሚያምኑ ይናገራሉ፤ ሆኖም እውነተኛውን ቤዛነትና መንፈስ ቅዱስን አያውቁም፡፡ መንፈስ ቅዱስን እንድትቀበሉ የሚያደርጋችሁን እውነተኛ ወንጌል ታውቃላችሁን? እግዚአብሄር በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞላችሁ ልትጠይቁት ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማወቅና በእርሱም ማመን አለባችሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ በአለም ዙሪያ ያሉት ክርስቲያኖች በሙሉ በሐጢያቶቻቸው ስርየት አማካይነት መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ እንደሚመራቸው የተረጋገጠ ነው፡፡

LanguageKiswahili
PublisherPaul C. Jong
Release dateApr 21, 2024
ISBN9798224129942
መንፈስ ቅዱስን የሚያገኙበት እርግጠኛውና ትክክለኛው መንገድ: በእኔ ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ

Related to መንፈስ ቅዱስን የሚያገኙበት እርግጠኛውና ትክክለኛው መንገድ

Related ebooks

Reviews for መንፈስ ቅዱስን የሚያገኙበት እርግጠኛውና ትክክለኛው መንገድ

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    መንፈስ ቅዱስን የሚያገኙበት እርግጠኛውና ትክክለኛው መንገድ - Paul C. Jong

    paul_Am03_cover.jpgFrontflap_Am03.gif1st_page

    በእኔ ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ

    መንፈስ ቅዱስን የሚያገኙበት እርግጠኛውና ትክክለኛው መንገድ

    Smashwords Edition

    የታተመው 2012 Hephzibah Publishing House

    ሙሉ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ ከዚህ መጽሐፍ ባለቤት በጽሁፍ የተገኘ ፈቃድ ሳይኖር የዚህን መጽሐፍ ማንኛውንም ክፍል ማባዛት ወይም በማንኛውም መልኩ ወይም በማንኛውም መንገድ በኤሌክትሮኒክ ወይም በሜካኒካል ፎቶ ኮፒ ማድረግን ጨምሮ በቅጂ መልክ ወይም መረጃን ይዞ በሚያጠራቅም ወይም መረጃን ይዞ በሚያስቀር ማንኛውም መንገድ ማሰራጨት አይቻልም፡፡

    ጥቅሶቹ በሙሉ የወሰዱት ከ1954ቱ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

    ISBN 978-89-6532-727-1

    ምሥጋና

    ከሰይጣን ሹክሹክታና ግፊቶች ላዳነን ጌታ ምስጋናን እሰጣለሁ፡፡ ለዚህ መጽሐፍ ሕትመት ራሳቸውን ቀድሰው ለሰጡ ከታች ለተዘረዘሩት አገልጋዮች አጋር ሰራተኞቼንና ለቅዱሳን ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን መግለጥ እወዳለሁ፡፡

    ሬቨረንድ ጆን ሺን

    ሃዩን-አህ ቾይ

    ሳንግ-ሚን ሊ

    ሮስ ዋላስ

    አንቶኒ ባንክስ

    ይህ መጽሐፍ ቀደም ያሉትን ሁለቱን የታተሙ መጽሐፎቼን ተከትሎ የመጣ የክትልል ሲሪየስ ተከታይ ነው፡፡ እንደገናም የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ለማረጋገጥና የዲያብሎስንም ሥራ ከክሊኒካዊና ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ አቋም አንጻር ይበልጥ በግልጽ ለማብራራት ሞክሬያለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ በመላው አለም በሚኖሩ ክርስቲያኖች ሁሉና በሰይጣን ከተታለሉ በኋላ በተቸገሩትና በሚያለቅሱት ሰዎች እንደሚነበብ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ አገልጋዮችና ምዕመናንንም ሳይቀሩ የሰይጣን ስራ እስከዚህ ዘመን ድረስ መኖር መቀጠሉን በሚመለከት የላቀ ግንዛቤ ላይ እንደሚደርሱ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

    በአንድ ወቅት ኢየሱስን በሚያስመስል አጋንንት ከተታለልሁ በኋላ በእጅጉ ተሰቃይቼ ነበር፡፡ ጌታ ግን የውሃውንና የመንፈስ ወንጌልን ለእኔ በመስጠት በዚህ አጋንንት ከተፈጠሩት ውሸቶችና ሰቆቃ አዳነኝ፡፡ ስለዚህ ሰይጣን ሥራውን ለማሳለጥ የኢየሱስን ስም እንደሚጠቀም በመግለጥ የእርሱን ሥራ እንድሰራ ለፈቀደልኝ ጌታ ምስጋናን አቀርባለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ እኔም በአንድ ወቅት እንደገጠመኝ በሐሰተኛ አመኔታ ስር እየተሰቃዩ ላሉ ሰዎች ነን፡፡ ክብርን ሁሉ ለእግዚአብሄር ስጡ፡፡

    PAUL C. JONG

    መቅድም

    የዓለም የክርስቲያን እምነት መለወጥ ይገባዋል፡፡ በክርስትና ውስጥ በእጅጉ ተዘውትረው ለውይይት የሚቀርቡት ርዕሰ ጉዳዮች ‹‹ከሐጢያት መዳን›› እና ‹‹ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ›› ናቸው፡፡ ሁለቱ እጅግ አስፈላጊ እሳቤዎች እነዚህ ቢሆኑም ሰለ እነዚህ ሁለት እሳቤዎች ግልጽ የሆነ እውቀት ያላቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው፡፡ ሰዎች የመጀመሪያ የሆኑትን የቤዛነትና የመንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት ሳያውቁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያምኑ ለመናገር ይደፍራሉ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ ለሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች መልሶች እንዲሆኑ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ በሚመለከት ይህንን መጽሐፍ ለመጻፍ መንፈስ ቅዱስን የተቀበልነውን ሰዎች ጠርቶናል፡፡

    ምንም እንኳን በኢየሱስ ክርስቶስ የማምን አማኝ የነበርሁ ብሆንም በአንድ ወቅት በሕግ በመታዘር ስሜት ስሰቃይ ነበር፡፡ ሆኖም እግዚአብሄር ውብ የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንድገነዘብ አደረገኝና የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ሰጠኝ፡፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በአመታት ውስጥ በፍጥነት አድገዋል፤ ነገር ግን ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደሚገኝ የሚያውቁ ሰዎች በጣም ጥቂት ስለሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት መንፈስ ቅዱስን ስለመቀበል ትክክለኛው መንገድ ምን እንደሆነ ለመጻፍ ወሰንሁ፡፡

    በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ውብ የሆነው ወንጌል የሚጠቁመው ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስን የሚለግሰንን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ነው፡፡

    መንፈስ ቅዱስን ሊለግሳችሁ የሚችለውን የውሃና የመንፈስ ወንጌል ታውቃላችሁን? በእርግጥ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል የምትመኙ ከሆነ ስለዚህ ጉዳይ በመጀመሪያ እርግጠኛና ትክክለኛ እውቀት ልታገኙ ይገባል፡፡ መንፈስ ቅዱስን እንድትቀበሉ የሚረዳችሁን ወንጌል ታውቁታላችሁን? እግዚአብሄርን ስለ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ መጠየቅ የምትፈልጉ ከሆነ በመጀመሪያ ስለ መንፈስ ቅዱስ ትክክለኛ እውቀት ልታገኙና በእርሱም ላይ እምነት ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ ታዲያ መንፈስ ቅዱስን እንድትቀበሉ የሚያስችላችሁ ቁልፍ የሆነው መስፈርት ምንድነው? ውብ በሆነው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ከሐጢያቶቻችሁ በሙሉ መንጻት ነው፡፡ ይህንን እንድታደርጉ ለመርዳትም ትክክለኛውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እውቀት ወደ እናነተ ማስተላለፍ እወዳለሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስን የምትቀበሉት ይህንን እውቀት ስትቀበሉ ብቻ ነው፡፡

    በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተብራራው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ከድማሚት ጋር እኩል የሆነ ሐይል አለው፡፡ አንድ ድማሚት ሚፈነዳበት ጊዜ አንድ ሙሉ ሕንጻ ሊፈርስ ይችላል፡፡ ልክ እንደዚሁ ወንጌልም የአማኞችን ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ያፈነዳል፡፡ እናንተ በዚህ እውነት የምታምኑ ሰዎች በእርግጠኝነት ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ትቀበላላችሁ፡፡ ጌታ ለሰው ዘር ሁሉ የሰጠው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እውቀት የመንፈስ ቅዱስን በረከት አምጥቶላችኋል፡፡ በጽሁፎቼ ውስጥ ውብ የሆነውን ወንጌል ጨምራችሁ በብዙ ትማራላችሁ፡፡ በተጨማሪም በዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ሆናችሁ ትኖራላችሁ፡፡ ከዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ለሚፈልቀው የሕይወት ውሃ ምስጋና ይሁንና እናንተ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የምታውቁና የምታምኑ በሰላማዊና በደስታ ሕይወት ትኖራላችሁ፡፡

    በዘመናዊው ማህበረሰብ ውስጥ አብዣኞቹ ሰዎች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እውነት ስለማያውቁ ሐሰተኛ አስተማሪዎች በሰጡዋቸው የተሳሳቱ ምናቦች ስር ሆነው እየተሰቃዩ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ‹‹በመነቃቃት ስብሰባዎች›› ላይ ይሰበሰቡና በመድረኩ ላይ ያለው ሰባኪ ፈጣን ቅላጼ ያላቸውን መዝሙሮች ሲዘምርና ሰዎች ንስሐ እንዲገቡ ሲቀሰቅስ አቅላቸውን ስተው እያጨበጨቡ ይደሰታሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የገንዘብ አየር በሚነፍስባቸው በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ሰዎች ‹‹ጌታ!›› እያሉ ሶስት ጊዜ ይጮሁና ድምጻቸው እስኪደክም ድረስ እግዚአብሄር የመንፈስ ቅዱስን ሙላት እንዲሰጣቸው ይለምናሉ፡፡

    በእነዚህ ስበሰባዎች ላይ የሚገኙ ሰዎች ጸሎቶችን በማነብነብ ፋንታ ያለቅሳሉ፡፡ አየሩ የግለት ጫፍ ላይ ሲደርስ ሰዎች ይጮሁና በየማዕዘኑ ራሳቸውን ይስታሉ፡፡ ሆኖም በመድረኩ ላይ ያለው ሰባኪ ድምጽ ማጉያውን ወደ ከንፈሮቹ ያስጠጋና ሕዝቡን ይበልጥ ጥልቅ ወደሆነ ሐይማኖታዊ ጥራዝ ነጠቅነት ውስጥ እየመራ በማስገባት የነፋስ አይነት ድምጽን ያሰማል፡፡ እንግዳ በሆኑ ልሳኖች በመናገር ይጸልያል፤ በሰዎች ራሶች ላይ እጆቹን ለመጫንም ከመድረኩ ዘሎ ይወርዳል፡፡ አንዳንድ ሰዎች በእንግዳ ልሳኖች መናገር ይጀምራሉ፡፡ አንዳንዶችም ይንቀጠቀጡና ራሳቸውን ይስታሉ፡፡

    ከዚያም ከልክ ባለ ስሜት፣ ፍርሃት፣ አቅልን መሳትና መሻት መካከል ሕዝቡ ራሳቸውን እስከሚስቱ ድረስ በማይሰተዋል ቋንቋ (በልሳናተ መናገር ተብሎ በሚጠራ) መጸለይ ይጀምራሉ፡፡ አጋንንቶች ወደ ሰውነቶቻቸው ውስጥ የገቡ ይመስል አካላዊ እንቅጥቃጤዎችን ይለማመዳሉ፡፡ እንዲህ ያለው ልቅ ስሜትና አቅልን መሳት አንዳንድ ሰዎችን በተጨባጭ ወፈፌ ያደርጋቸዋል፡፡ እንዲህ ያለውን ክስተት ‹‹የጥርቅም ወፈፌነት በሽታ›› ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡

    ብዙ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ተስፋ በማድረግ ወደዚህ ሐይማኖታዊ ጥራዝ ነጠቅነት ተስበዋል፡፡ እነርሱ አቅልን ወደ መሳትና ወደ ወፈፌነት ደረጃ በመድረስ መንፈስ ቅዱስን እንደሚቀበሉ ያምናሉ፡፡ ነገር ግን እንዲህ ያለው ጥራዝ ነጠቅነት የሚመጣው ከሰይጣን ነው፡፡

    እነዚህ ሐይማኖታዊ ጥራዝ ነጠቆች ዘለቄታዊውን መንፈስ በሚመለከት ቅንጣት ያህል እንኳን በቃሎቹ ላይ ፍላጎት የላቸውም፡፡ ይልቁንም በአካላዊ ልምምዶቻቸውና በሐሰተኛ ሰባኪዎች አስተምህሮቶች ያምናሉ፡፡

    እኛ እነዚህን ምግባሮችና እነርሱን የሚመሰሉ ሌሎች ልምምዶችን ስንመረምር የዘመኑ ክርስትና አንድ ሰው ‹‹የጴንጤቆስጤ ካራዝማቲክ እንቅስቃሴ›› ወይም ከጥንታዊው ጥንቆላ የመጣው ‹‹ኒዮ ፔንቴኮስታሊዝም›› ተብሎ የሚገለጥ በሽታ እንደያዘው ማየት ይችላል፡፡ እነርሱ በዚህ የጥራዝ ነጠቅነት በሽታ የተያዙት ለምንድነው? ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስን መቀበል የሚገባቸው ውብ በሆነው የውሃና የመንፈስ ወንጌል በማመን ብቻ እንደሆነ የሚናገረውን እውነት ባለመቀበላቸው ነው፡፡

    እውነተኛው የውሃና የመንፈስ ወንጌል የተከወነው ኢየሱስ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ደሙ ነው፡፡ እምነታቸው እንዲህ ካለው ጥራዝ ነጠቅነት የተገኘ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንል ሳያምኑ መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደሚችሉ በተሳሳተ አንደምታ ውስጥ ናቸው፡፡ የእነርሱ እምነት ተብዬ ክርስትናን ተራ ወደሆነ አይረቤ ጥንቆላ ዝቅ አደረገው፡፡ ዛሬ እንዲህ አይነት ሐይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች በመላው አለም እየተሰራጩ ነው፡፡ ብዙ ክርስቲያኖችም የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ከአጋንንቶች ሥራ ለይተው መናገር ስለማይችሉ ግራ የተጋቡ ናቸው፡፡

    ‹‹መንፈስ ቅዱስ የሚያድረው በማን ውስጥ ነው?›› በመላው አለም ከሚገኙ አገልጋዮችና ሐይማኖታዊ ተመራማሪዎች ለረጅም ጊዜ መልስ እየጠበቀ ያለ ጥያቄ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ብዙ ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ ያላቸውን እውቀታቸውንና መረዳታቸውን ከፍ ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ሰዎችን ግራ የሚያጋባና በባዕድ አምልኮአዊ አመኔታዎች እንዲጠቁ ከማድረግ በቀር የፈየደላቸው ነገር የለም፡፡ ይህ ችግር የጀመረው በ19ኛው ምዕተ አመት መጀመሪያ ላይ ከዳበረው የጴንጤቆስጤ-ካራዝማቲክ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴ መላውን ዓለም ጠራርጎታል፡፡ ነገር ግን የክፉ መናፍስቶች ስራ ነበር፡፡ ራሳቸውን በተሳሳተ መንገድ ክርስቲያኖች ብለው የቆጠሩ ቡድኖችን ጨብጦዋል፡፡

    በዓለም ሁሉ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ወደ እርሱ ቃሎች መመለስና ለጥያቄዎቻቸውም መልሶችን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ውስጥ ማግኘት አለባቸው፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖችን ለመርዳትም በጥንቷ ቤተክርስቲያን የሆነውን የመንፈስ ቅዱስ ስራ አብራራለሁ፡፡ እንደዚሁም ‹‹በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል›› እና ‹‹በዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ›› መካከል ያለውን ዝምድና እዘረዝራለሁ፡፡

    ከሁሉም በላይ ‹‹በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ደም››በሚያምኑ ሰዎች ውስጥ ያለውን የዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ እሳቤ ግልጽ አደርጋለሁ፡፡

    ዛሬ ብዙ ክርስቲያኖች ይህንን የዘለቄታዊውን ምፈስ ቅዱስ ቁልፍ እሳቤ በተሳሳተ መንገድ ተረድተውታል፡፡ ሐጢያቶቹ ይቅር ያልተባሉለት ሰው እንኳን መንፈስ ቅዱስን ሊቀበል ይችላል በማለት በግትርነት ያምናሉ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ቃሎች ሳያምኑ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ መቀበል አይቻልም፡፡ ሆኖም ብዙ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እምነት ሳይኖር በኢየሱስ ማመን ብቻ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል እንደሚያስችላቸው ያስባሉ፡፡

    በውስጣችን የሚያድረው መንፈስ ቅዱስ ይሁን ወይም የአጋንንት መንፈስ ለይተን ለማወቅ የእርሱን ቃሎች ማጥናት አለብን፡፡ ምን ታስባላችሁ? በኢየሱስ ብታምኑም ሐጢያት ካለባችሁ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ ይኖራል ብላችሁ ታስባላችሁን? በውስጣችሁ ያለው መንፈስ መንፈስ ቅዱስ ለመሆኑ እርግጠኞች ናችሁን?

    እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ እንዲኖር የሚፈቅደው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምን እምነት ሲኖራችሁ ብቻ የመሆኑን እውነት ማወቅ አለባችሁ፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ከሙሉ ልባችሁ የውሃውና የመንፈሱን ወንጌል ማወቅና ማመን አለባችሁ፡፡ ፍጹም በሆነ እርግጠኝነት ይህ እውነት እንደሆነ ልነግራችሁ እችላለሁ፡፡ እኔ አሁን እየተረክሁላችሁ ያለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት የምትቀበሉ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ በእርግጠኝነት በውስጣችሁ ያድራል፡፡

    ከሙሉ ልባችሁ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እንድታምኑ ልነግራችሁ እወዳለሁ፡፡ ያን ጊዜ ከጌታ ጋር ትገናኙና በዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ትባረካላችሁ፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች በዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ የተባረኩ ናቸው፡፡ ጌታም በሰማይ እያንዳንዱን መንፈሳዊ በረከት ይለግሳቸዋል፡፡ ጌታ በዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ይባርካችሁ፡፡

    የማውጫ ሰሌዳ

    መቅድም

    ክፍል አንድ--ስብከቶች

    1. መንፈስ ቅዱስ የሚሰራው በእግዚአብሄር የተስፋ ቃል ውስጥ ነው (የሐዋርያት ሥራ 1፡4-8)

    2. ማንም ሰው በግል ጥረቱ መንፈስ ቅዱስን ሊገዛ ይችላልን? (የሐዋርያት ሥራ 8፡14-24)

    3. በኢየሱስ ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀብላችኋልን? (የሐዋርያት ሥራ 19፡1-3)

    4. እነዚያ ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ጋር ተመሳሳይ የሆነ እምነት ያላቸው ሰዎች (የሐዋርያት ሥራ 3፡19)

    5. ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁን? (1ኛ ዮሐንስ 1፡1-10)

    6. መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ እንደሚኖር እመኑ (ማቴዎስ 25፡1-12)

    7. መንፈስ ቅዱስ በልባችሁ ውስጥ እንዲያድር የሚፈቅድላችሁ ውብ ወንጌል (ኢሳይያስ 9፡6-7)

    8. የመንፈስ ቅዱስ የሕይወት ውሃ የሚፈስሰው በእነማን ውስጥ ነው? (ዮሐንስ 7፡37-38)

    9. ንጹህ ያደረገን የኢየሱስ ጥምቀት ወንጌል (ኤፌሶን 2፡14-22)

    10. በመንፈስ ተመላለሱ! (ገላትያ 5፡16-26፤6፡6-18)

    11. ሕይወታችሁን በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ አድርጎ ለመጠበቅ (ኤፌሶን 5፡6-18)

    12. በመንፈስ ቅዱስ የተሞላውን ሕይወታችሁን ለመኖር (ቲቶ 3፡1-8)

    13. የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎችና ስጦታዎች (ዮሐንስ 16፡5-11)

    14. መንፈስ ቅዱስን ወደ ማግኘት የሚመራን ትክክለኛው ንስሐ ምንድነው? (የሐዋርያት ሥራ 2፡38)

    15. መንፈስ ቅዱስን መቀበልና በእርሱም መኖር የምትችሉት እውነቱን ስታውቁ ብቻ ነው (ዮሐንስ 8፡31-36)

    16. መንፈስ ቅዱስን ያገኙ ሰዎች ተልዕኮ (ኢሳይያስ 61፡1-11)

    17. በመንፈስ ቅዱስ እምነትና ተስፋ ሊኖረን ይገባል (ሮሜ 8፡16-25)

    18. መንፈስ ቅዱስን እንድትቀበሉ የሚመራችሁ እውነት (ኢያሱ 4፡23)

    19. የቤተ መቅደሱን መጋረጃ የቀደደው ውብ ወንጌል (ማቴዎስ 27፡45-54)

    20. እነዚያ መንፈስ ቅዱስን ያገኙት ሌሎች መንፈስ ቅዱስን ያገኙ ዘንድ ይመራሉ (ዮሐንስ 20፡21-23)

    ክፍል ሁለት -- አባሪ

    1. የደህንነት ምስክርነቶች

    2. ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

    Sermon0101

    መንፈስ ቅዱስ የሚሰራው በእግዚአብሄር የተስፋ ቃል ውስጥ ነው

    << የሐዋርያት ሥራ 1:4-8 >>

    ‹‹ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፡፡ ነገር ግን፡- ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፤ ዮሐንስ በውሃ አጥምቆ ነበርና እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ፡፡ እነርሱም በተሰበሰቡ ጊዜ፡- ጌታ ሆይ በዚህ ወራት ለኢየሩሳሌም መንግሥትን ትመልሳልህን? ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም፡- አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ሐይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምም፣ በይሁዳም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፡፡››

    በአንድ ወቅት ስጸልይ ሳለ ልክ መንፈስ ቅዱስን የሚመስል የአንድ ነገር ነበልባሎችን የመቀበል ልምምድ አገኘሁ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ነበልባሎች በተጠራቀመው ሐጢያት ፊት በነው ጠፉ፡፡ ሆኖም በውስጣችን ለዘላለም ስለሚኖረው መንፈስ ቅዱስ እውነቱን ላሳያችሁ እፈልጋለሁ፡፡ ይህንን የማሳያችሁ በቀላሉ በሐሰት መንፈስ የሚጠፋውን ሳይሆን በእውነተኛው ወንጌል አማካይነት የሚነደውን ነው፡፡ በዚህ መልዕክት በኩል የማስተዋውቃችሁ መንፈስ ቅዱስ በጸሎቶች አማካይነት ስለምትቀበሉት ሳይሆን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ባላችሁ እምነት ብቻ የምትቀበሉትን መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡

    በዚህ መጽሐፍ አማካይነት [1]በውስጣችሁ የሚኖረውን መንፈስ ቅዱስ እንድትቀበሉ እመራችኋለሁ፡፡ ለእናንተ የማቀርበው መልዕክት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የመጣ መሆኑንም ትገነዘባላችሁ፡፡ በዚህ ወቅት መንፈስ ቅዱስን እንቀበል ዘንድ የእግዚአብሄር ፍጹም ፍላጎት ነው፡፡ በውስጣችሁ ስለሚያድረው መንፈስ ቅዱስ መማርና በዚህ መጽሐፍ አማካይነት መቀበል ትችላላችሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ ለእናንተ በቂ ካልሆነ ቀደም ብዬ ያሳተምኋቸውን ሁለቱን መጽሐፎቼን እንድታነቡ እመክራችኋለሁ፡፡ በእነዚህ መጽሐፎች አማካይነት በእግዚአብሄር ፊት ፍጹም እምነትን ትቀበላላችሁ፡፡

    ================

    [1] መንፈስ ቅዱስ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ይቅርታን ባገኙ ዳግም የተወለዱ ልቦች ውስጥ ይኖራል፡፡ መንፈስ ቅዱስ አንድ ጊዜ በቅዱሳኑ ውስጥ ከገባ በውስጣቸው ለዘላለም ይኖራል፡፡ በወንጌል እስካመኑ ድረስም ትቶዋቸው አይሄድም፡፡ ለቅዱሳን አመኔታን ይሰጣቸዋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሄር ፈቃድ እንዲያውቁ ይመራቸዋል፡፡ በአለም ውስጥ ያሉትን ፈተናዎችና ችግሮች እንዲያሸንፉ ያበረታቸዋል፡፡ የመንፈስ ፍሬዎችንም አብዝተው እንዲያፈሩ ይፈቅድላቸዋል፡፡ እግዚአብሄር በውስጣቸው በሚያድረው መንፈስ ቅዱስ አማካይነት የቅዱሱን አካል የእግዚአብሄር መቅደስ አድርጎ ያከብረዋል፡፡ (የሐዋርያት ሥራ 2፡38-39፤ ዮሐንስ 14፡16፣ 16፡8-10፤1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16፣ 6፡19፤ገላትያ 5፡22-23)

    ================

    ብዙ ክርስቲያኖች በበዓለ ሃምሳ ቀን በኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ላይ እንደወረደው መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ይሞክራሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህን ዘዴ በመጠቀም ብዙ ገንዘብ አከማችተዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሰው ጥረት የሚገኝ ነገር እንደሆነ አድርገው ያታልላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ራዕዮችን ማየት፣ ተዓምራትን ማድረግ፣ የኢየሱስን የራሱን ድምጽ መስማት፣ በልሳን መናገር፣ ሕሙማንን ማዳንና አጋንንትን ማስወጣት ይፈልጋሉ፡፡ ሆኖም በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ያላባቸው ስለሆኑ በክፉ መናፍስት ተጽዕኖ ስር ናቸው፡፡ (ኤፌሶን 2፡1-2) አሁንም እንኳን ብዙ ሰዎች በክፉ መናፍስት ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ሳያውቁ በመኖር ላይ ናቸው፡፡ ሰይጣን እንደ ድንቆችንና ተአምራቶች ያሉ ዘዴዎችን በመጠቀም ሰዎችን የሚያስተውና የሚያታልለው ለዚህ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ምናብ ናቸው፡፡

    ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ በማለት አዘዛቸው፡- ‹‹ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፡፡ ነገር ግን፡- ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 1፡4) በሐዋርያት ሥራ ላይ ያለው መንፈስ ቅዱስ የተገኘው ‹‹በሥራ››፤ ‹‹በልምድ›› ‹‹በመሰጠት›› ወይም ‹‹በጸሎት›› ሳይሆን ‹‹የእግዚአብሄርን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ነው፡፡›› ከዚህ ምንባብ መማር የምንችለው ነገር ቢኖር መንፈስ ቅዱስ በሰው ልጆች በሚደረግ ተደጋጋሚ ጸሎት ሊገኝ እንደማይችል ነው፡፡ ይህ እግዚአብሄር አብና ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ዘር በሰጡት ውብ የውሃና የመንፈስ ወንጌል ሙሉ በሙሉ በማመን ብቻ የሚገኝ የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡ እውነተኛውን መንፈስ ቅዱስ ማግኘት የሚቻለውም ኢየሱስ ክርስቶስ በሰጠን ወንጌል ላይ ባለን እምነት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር በውስጣችን የሚያድረውን መንፈስ ቅዱስን በትክክል ለማግኘት እንችል ዘንድ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሰጥቶናል፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 3፡3-5)

    ‹‹የመንፈስ ቅዱስ ተስፋ›› የሚለው ሐረግ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በተደጋጋሚ ተጽፎአል፡፡ ጴጥሮስ በበዓለ ሐምሳ ቀን ስለወረደው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በመልዕክቱ ላይ እንደተናገረው (የሐዋርያት ሥራ 2፡38-39) ‹‹በውቡ የውሃና የመንፈስ ወንጌል አምነው የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ ላገኙ መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሄር የሚሰጥ ስጦታ ነው፡፡››

    በውስጣችን የሚያድረው መንፈስ ቅዱስ የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ ላገኙት የሚሰጥና የእግዚአብሄርን ተስፋ ፍጻሜ ትርጉም የያዘ ስጦታ ነው፡፡ በአዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሄርና በሰዎች መካከል በተደረገ ስምምነት ሊሰጥ የሚችል አንዳች ነገር ሳይሆን ከእግዚአብሄር የመጣ ተስፋ የተሰጠበት ስጦታ ነበር፡፡ ስለዚህ በውስጣችሁ የሚያድረው መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ ውስጥ እንደተገለጠው በጸሎት አማካይነት ሊገኝ የሚችል ስጦታ አይደለም፡፡ (የሐዋርያት ሥራ 8፡19-20)

    መንፈስ ቅዱስ የሚወርደው ኢየሱስ በሰጠን የውሃና የመንፈሱ ወንጌል በሚያምኑት ላይ ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በውስጣቸው መንፈስ ቅዱስ እንዲኖር መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክ ቃል ገብቶላቸው ነበር፡፡ ‹‹ዮሐንስ በውሃ አጥምቆ ነበርና እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 1፡5) ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ የእግዚአብሄር የተስፋ ቃል እስኪፈጸም ድረስ ጠበቁ፡፡

    በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ ሰዎች ያምኑዋቸው የነበሩትን እምነቶች ስንመለከት ይህን ያገኙት በእግዚአብሄር ስጦታ እንጂ በራሳቸው ጥረት አለመሆኑን ማየት እንችላለን፡፡ በሐዋርያት ሥራ ላይ መንፈስ ቅዱስ በደቀ መዛሙርቱ ላይ የወረደው በሰብአዊ ጥረት ወይም በመንፈሳዊ ስኬት አልነበረም፡፡

    በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተጻፈው የመንፈስ ቅዱስ በደቀ መዛሙርቱ ላይ መውረድ እውን ሆነ፡፡ ይህም ልክ ኢየሱስ ‹‹ከጥቂት ቀናት በኋላ›› ብሎ እንደተናገረው ነበር፡፡ ይህ በጥንቷ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው በረከት ነበር፡፡ ቅዱሳት መጻህፍትን በመመልከት የእግዚአብሄር ተስፋ የተፈጸመው በኢየሱስ በማመን እንጂ በዖም፣ በጸሎቶች ወይም ራስን መስዋዕት በማድረግ እንዳልሆነ ማየት እንችላለን፡፡ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ምዕመናን የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ አግኝነተው በዚያው ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፡፡

    መንፈስ ቅዱስ ድንገት በኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ላይ ከሰማይ ወረደባቸው!

    ‹‹በዓለ ሃምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 2፡1) የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክላቸው የገባውን ቃል እንዲፈጸም በአንድነት ተሰብስበው ነበር፡፡ በመጨረሻም መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው፡፡

    ‹‹ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ፡፡ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሞላው፡፡ እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፡፡ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 2፡2-4)

    መንፈስ ቅዱስ ‹‹በድንገት ከሰማይ›› ወረደባቸው፡፡ እዚህ ላይ ‹‹ድንገት›› የሚለው ቃል ይህ በሰው ልጆች ፍላጎት የተደረገ አልነበረም ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም ‹‹ከሰማይ›› የሚለው ሐረግ የሚገልጠው መንፈስ ቅዱስ ከየት እንደሚመጣ ከማብራራቱም በላይ በውስጣችን የሚያድረው መንፈስ ቅዱስ በሰው ፈቃድ ወይም ጥረት ሊገኝ ይችላል የሚለውን እሳቤ ይቃረናል፡፡ አንዳንዶች ‹‹ከሰማይ›› የሚለውን ቃል መንፈስ ቅዱስ የሚመጣው በጸሎት ነው በሚል ሰዎችን ለማታለል ይጠቀሙበታል፡፡

    በሌላ አነጋገር መንፈስ ቅዱስ በድንገት ከሰማይ መጣ ሲባል መንፈስ ቅዱስ በልሳን እንደ መናገር ወይም ራስን መስዋዕት እንደ ማድረግ ባሉ ምድራዊ ዘዴዎች ይመጣል ማለት አይደለም፡፡ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በመጀመሪያ በልሳን የተናገሩት ውቡን ወንጌል ከየአገሩ ለመጡ ሁሉ ለማሰራጨት ነበር፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ አማካይነት የውጪ ቋንቋ ለሚናገሩት አይሁድ ተናጋሪዎች በራሳቸው ቋንቋ ወንጌልን ለማሰራጨት ነበር፡፡ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡት ሰዎችም ደቀ መዛሙርቱ በገዛ ራሳቸው ቋንቋዎች በልሳን መናገራቸውን ሲሰሙ ነገሩ እንግዳ ነው ብለው አሰቡ፡፡ ምክንያቱም ከደቀ መዛሙርቶቹ አብዛኞቹ የገሊላ ሰዎች ነበሩና፡፡ 

    ‹‹እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፡፡ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 2፡3-4) እዚህ ላይ መንፈስ ቅዱስ ‹‹በያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጠባቸው›› ለሚለው ሐረግ ልዩ ትኩረት መስጠት አለብን፡፡ አንድ ቦታ ተሰብስበው የመንፈስ ቅዱስን መምጣት ይጠባበቁ የነበሩት ደቀ መዛሙርት በሙሉ ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ዳግም የመወለድን ወንጌል ቀድሞውኑም ያመኑ ነበሩ፡፡

    በዚህ ዘመን ያሉ ብዙ ክርስቲያኖች ይህን የመልዕክት ክፍል በትክክል አልተረዱትም፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ሆኖ የመጣው ሲጸልዩ በነበረ ጊዜ ነው ብለው አምነዋል፡፡ ሆኖም ስለ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ያለው የተሳሳተ መረዳት የመጣው ከድንቁርናና ከግራ መጋባት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ላይ ሲመጣ እንደዚህ ያለ ድምጽ ይፈጥራልን? የለም አይፈጥርም፡፡

    ሰዎች በጆሮዎቻቸው የሚሰሙት ድምጽ ሰይጣን የሰዎችን ነፍሶች በሚውጥበት ጊዜ የሚፈጥረውን ድምጽ ነው፡፡ እርሱ ይህንን ድምጽ የሚፈጥረው መንፈስ ቅዱስን ተመስሎ ሰዎችን ግራ መጋባት ውስጥ ለመክተት በሚያደርጋቸው ጥረቶቹ በምናቦች፣ በአስመሳይ ድምፆችና በሐሰተኛ ተአምራቶች በሚሰራበት ጊዜ ነው፡፡ ሰዎች እነዚህን ነገሮች የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ማስረጃ እንደሆኑ አድርገው በማሰብ ይሳሳታሉ፡ አንዳንድ ሰዎችም መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ እንደ ነፋስ አይነት ‹‹ሽሽሽ…›› የሚል ድምጽ እንደሚፈጥር ያስባሉ፡፡ እነዚህ በሰይጣን እየተታለሉ ነው፡፡ በሐዋርያት ስራ ውስጥ እንደተጻፈው መንፈስ ቅዱስ ሊገኝ የሚችለው በውቡ ወንጌል ላይ ባለን እምነታችን ብቻ ነው፡፡ 

    የጴጥሮስ እምነት (1ኛ ጴጥሮስ 3፡21) መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ይፈቅድለት ዘንድ ፍጹም ነበር፡፡ 

    በሐዋርያት ሥራ ላይ የተጻፉትን የበዓለ ሃምሳ ክስተቶች በማሰማመር እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ የወረደው አስቀድመው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመናቸው የመሆኑን እውነት ማበከር ፈለገ፡፡ ነገር ግን ሰዎች ብዙውን ጊዜ ‹‹በዓለ ሃምሳን›› መንፈስ ቅዱስ ከልዕለ ተፈጥሮ ምልክቶችና ከአሸባሪ ድምጽ ጋር ከሰማይ የወረደበት ጊዜ እንደነበር ያስባሉ፡፡

    በአሁኑ ጊዜ በመነቃቃት ጉባኤዎች ሰው በትጋት በመጸለይ፣ በመጾም ወይም ደግሞ በእጆች በመጫን መንፈስ ቅዱስን ማግኘት እንደሚችል የታመነው ለዚህ ነው፡፡ በአጋንንት መያዝ፣ ራስን መሳት፣ ለብዙ ቀናት ያህል ምናብ ውስጥ መቆየት ወይም ደግሞ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ መንቀጥቀጥ የመንፈስ ቅዱስ ስራዎች አይደሉም፡፡

    መንፈስ ቅዱስ ሚዛናዊ አካል ስለሆነ የሰውን ማንነት ችላ የሚል አይደለም፡፡ በሰው ላይ በዕብሪት አይወርድም፡፡ ምክንያቱም እርሱ እውቀት፣ ስሜትና ፈቃድ ያለው ሕላዌ እግዚአብሄር ነውና፡፡ እርሱ በሰዎች ላይ ሊወርድ የሚችለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሲያምኑ ብቻ ነው፡፡ (የሐዋርያት ሥራ 2፡38)

    ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ በደቀ መዛሙርቱ ላይ የመጣው ነቢዩ ኢዩኤል በተነበየው መልኩ መሆኑን መስክሮዋል፡፡ ይህም ሐጢያታቸው የተሰረየላቸው መንፈስ ቅዱስን ያገኛሉ የሚለውን በእግዚአብሄር የተሰጠ ተስፋ የሚፈጽም ነው፡፡ በሌላ አነጋገር መንፈስ ቅዱስን ማግኘት የሚችሉት ኢየሱስ የሰውን ልጆች ከሐጢያት ለማዳን መጠመቁንና መሰቀሉን የሚያምኑት ብቻ ናቸው፡፡ የጴጥሮስ ስብከት ከኢዩኤል ትንቢት ጋር አብሮ ኢየሱስ ለምን እንደተጠመቀና እኛም ይህን ማወቅ ለምን በዚህ ማመን እንደሚያስፈልገን ያሳየናል፡፡ ይህንን እውነት ማወቅ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ይመራቸዋል፡፡

    ጴጥሮስ በመሰከረለት ውብ ወንጌል ታምናላችሁን? ወይስ አሁንም ድረስ ከዚህ ውብ ወንጌል ጋር የማይገናኙ አይረቤና ከባዕድ አምልኮ ጋር የተያያዙ አመኔታዎችን ይዛችኋል? ያለ እግዚአብሄር ዕቅዶች መንፈስ ቅዱስን በራሳችሁ አድራጎት ለመቀበል ትሞክራላችሁን? (1ኛ ጴጥሮስ 3፡21) ሰዎች ከሐጢያቶቻቸው ለመንጻት ተስፋ በማድረግ በእግዚአብሄር ቢያምኑና የንስሐ ጸሎቶችን ቢያቀርቡም መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ከማመን በስተቀር ሌላ መንገድ የለም፡፡

    የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ባታውቁም አሁንም በውስጣችሁ የሚያድረውን መንፈስ ቅዱስ እየተጠባበቃችሁ ነውን? መንፈስ ቅዱስ በልባችሁ ውስጥ እንዲኖር የሚያደርገውን የኢየሱስን ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰውን ደሙን እውነተኛ ትርጉም ታውቃላችሁን? መንፈስ ቅዱስ በልባችሁ ውስጥ ሊያድር የሚችለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስታምኑ ብቻ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ እውነተኛው መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው እንዲኖር የተፈቀደላቸው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ዳግም የተወለዱት ብቻ ናቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስን እንድንቀበል የሚፈቅድልንን የውሃና የመንፈስ ወንጌሉ ስለሰጠን እግዚአብሄርን

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1